loading
የአፍሪካ ቀንድን የሚያስተሳስረው የልህቀት ማእከል ዕውን ሊሆን ነው…

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3፣ 2013 የአፍሪካ ቀንድን የሚያስተሳስረው የልህቀት ማእከል ዕውን ሊሆን ነው… በኮምቦልቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ550 ሚሊዮን ብር በጀት የምስራቅ አፍሪካ የቴክኒክ ትምህርትና ስልጠና የልህቀት ማዕከል ግንባታ ተጀመረ፡፡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ በማስጀመሪያ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደገለጹትበኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ የበለጸገ ብቁ ዜጋ ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡ ሚንስትሩ ለግንባታው ከ550 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ እንደሚደረግበት ጠቁመው፤ “በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ መንግስት ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል” ብለዋል።

በኮምቦልቻ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ የሚገነባው ማዕከል ሲጠናቀቅ ከምስራቅ አፍሪካ የተውጣጡ ተማሪዎች የሚማሩበት እንደሆነም ገልፀዋል። ማዕከሉ የተማሪዎች መማሪያ፣ ማደሪያ፣ መዝናኛና አስተዳደርን ጨምሮ 7 ህንጻዎች የሚኖሩት ሲሆን በመስራቅ አፍሪካ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካና በዓለም ተወዳዳሪ እንዲሆን በቅንጅት እንደሚሰራም ተነግሯል፡፡ የደቡብ ወሎ ዞን ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን መኮነን ማዕከሉ
በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅና ዓላማው እንዲሳካ ዞኑ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

የኮምቦልቻ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዲን አቶ መላኩ አራጋው በበኩላቸው ከዚህ በፊት የሰራናቸው ተግባራት የቴክኖሎጂ ፈጠራ ማዕከሉ በኮሌጃችን እንዲገነባ እድል ፈጥሯል ብለዋል፡፡ የቴክኒክ ትምህርቶች በተግባር ታግዘው የሚሰጡበት በመሆኑ አገልግሎቱን በቅርበት ለማግኘትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ ማዕከሉ ዓይነተኛ ሚና እንደሚኖረውም አብራርተዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *