loading
ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ጊዜያዊ ስምምነት ለማድረግ ጠየቀች፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8፣ 2013 ሱዳን ከኢትዮጵያነ ጋር በግድቡ ዙሪያ ጊዜያዊ ስምምት ለማድረግ ዝግጁ ነኝ አለች፡፡ የሱዳኑ የውሃ ሚኒስትር ያሲር አባስ ካርቱማ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ዙር የውሃ ሙሌት ከመጀመሯ አስቀድሞ በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ጊዜያዊ ውል ማሰር አለብን ብለዋል፡፡ ሚንስትሩ እንደ ቅድመ ሁኔታ አድርገው ካነሷው ነጥቦች መካከልም ከአሁን ቀደም የደረስንባቸው ስምምነቶችና ቀጣይ የሚደረጉ የሶትዮሽ ድርድሮች እንደሚቀጥሉ ማረጋገጫ ማግኘት የሚሉት ይገኙበታል፡፡

ግብፅና ሱዳን ኢትዮጵያ አሳሪ ህጋዊ ስምምነት ሳትፈርም በመጭው ሀምሌ ወር ሁለተኛውን ዙር የግድቡን የውሃ ሙሌት እንዳትጀምር የፀጥታው ምክር ቤት ጣልቃ ገብቶ እንዲያደራድር ዳግም እንቅስቃሴ ጀምረዋል፡፡ ሁለቱ ሀገራት የውሃ ሙሌቱ ከስምምነት ውጭ መካሄድ የለበትም በሚለው ሀሳብ ከዚህ ቀደም
ቢስማሙም አባስ ሁለተኛው ዙር ሙሌት ከተከናወነ በኋላም ቢሆን ድርድሮች እዲቀጥሉ ጊዚያዊ ስምምነት ማድረግ እንፈልጋለን ማለታቸው በሱዳን በኩል የአቋም ለውጥ ያለ አስመስሎታል ተብሏል፡፡ አሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው ኢትዮጵያ በበኩሏ የግብፅና ሱዳን ስምምነት ቢኖርም ባይኖርም ሁለተኛውን ዙር የውሃ ሙሌት የማይቀር መሆኑን አቋሟን በግልፅ አሳውቃለች::

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *