loading
ናይጄሪያ ለ12 ዓመታት በዘለቀው ግጭት ከ300 ሺህ በላይ ህፃናት መገደላቸውን የተባበሩት በ መንግስታት ድርጅት ይፋ አደረገ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18፣ 2013 በሰሜናው ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል ለዓመታት በዘለቀው ግጭት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ቁጥራቸው ወደ 350 ሺህ ለሚጠጋ ህፃናት ሞት ምክንያት ሆኗል ብሏል ድርጅቱ፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው ከሟቾቹ መካከል የሚበዙት ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች መሆኑን በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡ ቦኩ ሃራም የተባለው ታጣቂ ቡድን እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2009 የተደራጀ ጥቃት ማድረስ ከጀመረ ወዲህ ከ2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ራሳቸውን ለማዳን ሲሉ ቀያቸውን ጥለው ተሰደዋል ነው የተባለው፡፡

ቦኩ ሃራም እንደ አወሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2016 ጀምሮ በሁለት የተከፈለ ቢሆን ጥቃቱን አጠናክሮ በመቀጠል በጎረቤት ቻድና ካሜሮን ጭምር አለመረጋጋት ፈጥሯል ተብሏል፡፡ በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ የግጭት ቀጠና በሆነው አካባቢ ከ13 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የሚኖሩ ሲሆን ከነዚህ መካከል ከ8 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት አስቸኳይ ድጋፍ የሚፈልጉ መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገልጿል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *