loading
የሰኔ ወር ዋጋ ግሽበት 24 ነጥብ 5 በመቶ ጭማሪ አሳየ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28፣ 2013 የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በየወሩ የሚያወጣው የዋጋ ግሽበት መረጃ ሁኔታ የሰኔ ወር 2013 ዓ.ም ካለው ጋር ሲነጻጸር በ24 ነጥብ 5 ከመቶ ጭማሬ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡

የሰኔ ወር 2013 ዓ.ም የምግብ ዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ28 ነጥብ 7 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በዳቦና እህሎች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ በያዝነው ወርም የቀጠለ ሲሆን

በተለይ የበቆሎና የገብስ ዋጋ በፍጥነት ጨምሯል ሲል በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

የሥጋ ፣የምግብ ዘይት ፣ ቅቤ፣ ቅመማ ቅመም ፣ በርበሬ እና ቡና የዋጋ ጭማሪ በዚህም ወር በመቀጠላቸው ለዋጋ ግሽበት ምጣኔ በፍጥነት መጨመር አስተዋጽኦ አድርገዋል።

በሌላ በኩል ምግብ ነክ ያልሆኑ ዝርዝሮች የዋጋ ግሽበት የሰኔ ወር 2013 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ19 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ለዚህም በአልኮልና ትምባሆ ልብስ እና ጫማ፤ የማገዶና ከሰል ፤የቤት መስሪያ እቃዎች፤ የቤት ኪራይ፣ሲሚንቶና የቤት ኪዳን ቆርቆሮ እንዲሁም ህክምና ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ እንደምክንያት እንደሚነሳ መግለጫው ተቁሟል፡፡

አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ወር ጋር ሲነጻጸር በ7 ከመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ማዕከላዊ እስታስቲክ ኤጀንሲ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *