loading
ኢትዮጵያ በጽናት ትገሰግሳለች-ጠ/ሚ ዐቢይ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 12፣ 2013  ጠ/ሚ ዐቢይ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ 2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩን አስመልክተው በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ኢትዮጵያ በጽናት ትገሰግሳለች ብለዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ÷የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት መርሃግብር በተሳካ ሁኔታ በመከናወኑ እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን አብሮ ደስ አለን ብለዋል። በቀጣይ የሃገራችንን የመልማት ፍላጎት ጥያቄን በሚመልስ መልኩ የጀመርነው ሁለንተናዊ የለውጥ ጉዞ በህዝባችን የነቃ ተሳትፎ እና ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ነው ያሉት።

ተፈጥሮ የሰጠችንን ታላቅ ፀጋ አልምተን ለመጠቀም በገንዘባችሁ፣ በጉልበታችሁ፣ በላባችሁና በዕውቀታችሁ ባደረጋችሁት ብርቱ ርብርብ ለዚህ ታሪካዊ ስኬት በመብቃታችን እንኳን ደስ አለን ብለዋል። በዚህ የስኬት ግለት ሃገራችንን ለውጪ አካላት ተጋላጭ የሚያደርጉ ሃይሎችን በተባበረ ክንድ መመከትና ሴራቸውን ማምከን ይገባልም ብለዋል። የታላቁ ህዳሴ ግድብ ታሪካዊ ፕሮጀክት በዚህ የስኬት ደረጃ ያደረሰ እንዲሁም በብዙ ጫናዎች ሳይበገር ሰላማዊ ምርጫ ያካሄደ ህዝብ አንድነቱን አጥብቆና ጠብቆ ሲተም ለውጤት እንደሚበቃ ትልቅ ማሳያ መሆኑን መመልከት ይቻላል ሲሉ ገልጸዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *