loading
የህወሓት ሽብር ቡድን እና የተላላኪዎቹ እቅድ በህዝቦች ህብረት ዛሬም ይከሽፋል- አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 የህወሓት ሽብር ቡድን እና የተላላኪዎቹ እቅድ በህዝቦች ህብረት ዛሬም ይከሽፋል- አቶ ሽመልስ አብዲሳ
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የሽብር ቡድኑ ህወሓት እና የተላላኪዎቹ እቅድ በህዝቦች ህብረት ዛሬም እንደሚከሽፍ ገለጹ፡፡
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በማብራሪያቸው ኢትዮጵያ በህወሓት እና በተላላኪዎቹ የምትፈርስ ሳትሆን በህዝቦቿ አንድነት ተገንብታ የምትሻገር ናት ነው ያሉት፡፡

አሸባሪው ህወሓት በኢትዮጵያውያን ላይ ከፍ ሲል በትግራይ ህዝብ ላይ በሚፈጽመው እኩይ ተግባር መጥፊያውን እያፋጠነ ነው ብለዋል፡፡ከትናንት ጀምሮ የዜጎችን ደም ሲያፈስ እንደኖረው ሁሉ በማይካድራ የፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲሁም በአፋር ክልል በንጹሀን ዜጎች በህጻናት እና ሴቶች ላይ የፈጸመው ድርጊት የአጥፍቶ ጠፊ ተግባሩ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ርዕስ መስተዳደሩ ከኦ ቢ ኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ለውድቀታችን በመስራት ላይ ያሉት የሽብር ቡድኑ እና የውጪ ሀገራት ተላላኪዎች እንደማይሳካላቸው ህዝቡ ሰሞኑን ለመከላከያ ሰራዊቱ ያሳየው ድጋፍ ምስክር ነው ብለዋል፡፡ የህወሓት ሽብር ቡድንን እና ተላላኪዎቹን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ በመደምሰስ የኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንደሚረጋገጥም ገልጸዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *