loading
በኒውዚላንድ አንድ የኮቪድ-19 ተጠቂ መገኘቱን ተከትሎ በሀገር አቀፍ ደረጃ ዕቀባ ተጣለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣2013 በኒውዚላንድ አንድ የኮቪድ-19 ተጠቂ መገኘቱን ተከትሎ በሀገር አቀፍ ደረጃ ገደብ መጣሉ ተነገረ፡፡በኒው ዚላንድ በስድስት ወር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ፤ ኦክላንድ ውስጥ አንድ ሰው የኮቪድ-19 ተህዋሲ ተጠቂ መሆኑን ሪፖርት መደረጉን ተከትሎ ከሶስት ቀን እስከ ሳምንት የሚደርስ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉ ታውቋል። በተህዋሲው የተያዘው ሰው የተጎበኘችው የባህር ዳርቻዋ ከተማ ኮሮማንዴል እንደ ኦክላንድ ሁሉ ለሰባት ቀናት በገደብ ውስጥ ትሆናለች ተብሏል።

በኮቪድ የተያዘው ሰው የ58 ዓመት ባለፀጋ ሲሆን ከባለፈው ሐሙስ ጀምሮ በበሽታው እንደተጠቃ ይታመናል፡፡ በዚህም ቢያንስ 23 የሚሆኑ የቫይረሱ ማስተላለፊያ አካባቢዎች ተለይተዋል ተብሏል። የሀገሬው ባለሥልጣናት አዲሱ የዴልታ ተዋህሲ ሊሆን ይችላል በሚል ግምት እየሠሩ መሆናቸውን
ቢቢሲ አስነብቧል። ከሀገሪቱ የሕዝብ መጠን 20 በመቶው ገደማ ሙሉ በሙሉ ክትባት ተሰጥቶታል የተባለ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን በጣም ከባድ የሆኑት ህግጋት መተግበር ያስፈልጋል በማለት ተናግረዋል ፡፡

በዚህም እጅግ ወሳኝ አገልግሎት ሰጪ ከሆኑ ተቋማት ውጪ ያሉት እንደ ትምህርት ቤቶች፣ ቢሮዎች እና ሌሎች የንግድ እንቅስቃሴዎች ይዘጋሉ ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሯ በጠንካራ ስራ፤ ፈጣን እርምጃ በመውሰድ ከአሁን ቀደም በተህዋሲው ላይ የተገኘውን ውጤት ማስጠበቅ እንደሚፈልጉ ገለጸው ነበር፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *