loading
ወርቅን በብር ቀይሮ ለማስቀመጥ በሚሰሩ አሻጥሮች አብዛኛው የወርቅ ምርት ባንክ እየገባ አደለም ተባለ።

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 17፣2013  ወርቅን በብር ቀይሮ ለማስቀመጥ በሚሰሩ አሻጥሮች አብዛኛው የወርቅ ምርት ባንክ እየገባ አደለም ተባለ። የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ይህንን ያሉት ከጋምቤላ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር የማዕድን ዘርፉ በሚጠናከርበት ዙሪያ በተወያዩበት ወቅት ነው። ፈቃድ በተሰጣቸው የወርቅ አዘዋዋሪዎች አስፈላጊውን ክትትልና ጥናት በማካሄድ እርምጃ መውስድ እንሚያስፈልግም ነው የገለጹት።

በጋምቤላ ክልል ያለውን የወርቅ ሀብት የአመራረትና ግብይት ሰንሰለት ለማዘመን ሚኒስቴሩ አስፈለጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን የተናገሩት ኢንጂነር ታከለ ለዘርፍ ማነቆ የሆኑ የአሰራርና የህግ ማቀፎችን ጭምር በማሻሻል ረገድ አመራሩ በቁርጠኝነት ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ከፋይናንስ ተቋማት ተደራሽነት አንጻር ለቀረቡ ችግሮች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ደረጀ ፉፋ የአካባቢውን ተጨባጭ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ተጨማሪ የባንክ ቅርንጫፎችን ለመክፋት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በጋምቤላ ክልል በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ1 ሺህ 213 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሄራዊ ባንክ ገቢ የተደረገ ሲሆን በተያዘው የስራ ዘመን ደግሞ 1 ሺህ 600 ኪሎ ግራም ወርቅ ለማስገባት መታቀዱን በውይይት መድረኩ ተገልጿል

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *