loading
ዓባይ ፀበላችን መብራታችን ለነፍስ ለስጋችንም የሚጠቅመን ሕይወታችን ነው-ብፁዕ አቡነ ናትናኤል::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2014 ዓባይ ፀበላችን መብራታችን ለነፍስ ለስጋችንም የሚጠቅመን ሕይወታችን ነው ሲሉ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ገለፁ፡፡የታላቁ ሕዳሴ ግድብን ግንባታን በስፍራው ተገኝተው ለመጀመሪያ ጊዜ ግድቡን የተመለከቱት የምዕራብ ሸዋና ምስራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ናትናኤል ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያን ከጨለማ ወደ ብርሃን እና ወደ ከፍታ የምትወጣበት፣ ኢትዮጵያዊያንን ያለምንም ልዩነት አንድ ያደረገና ማንንም የማይጎዳ ግድብ ነው ብለዋል፡፡

ግድቡን ለመጀመሪያ ጊዜ ማየታቸውን የገለጹት አቡነ ናትናኤል፤ በአካል ሲመለከቱት መደነቃቸውና እስካሁን ሲዋጣ የነበረው ገንዘብ ወደ ተግባር መዋሉን ያረጋገጠና  ወደፊትም መጠናከር ያለበት ነው ብለዋል። የህዳሴ ግድቡ ኢትዮጵያ ራሷን ለመለወጥ በራሷ የምትገነባው እንጂ ማንንም አገር
ለመጉዳት እንዳልሆነ ገልጸዋል።ግድቡ ተጠናቆ ለመጠቀም ከልጅ እስከ አዋቂ መላው ኢትዮጵያዊያን መረባረብ ይገባልምብለዋል። ዓባይ በመጽሐፍ ቅዱስ የተነገረለት ወንዝ መሆኑን ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያዊያን ደግሞ ስንዘምርለት የኖርን ምንጫችን፣ ፀበላችንም ጭምር ነው ብለዋል።

ታላቁ ህዳሴ ግድብ የሁላችንም ነው" ያሉት አቡነ ናትናኤል፤ ለፍጻሜው መትጋት እንደሚገባ ገልፀዋል። አቡነ ናትናኤል የ2014 ዓ.ም የሰላምና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን  አስተላልፈዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *