loading
የግል ባንኮች ለቀጣዩ ፉክክር ራሳችሁን አዘጋጁ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2014 በኢትዮጵያ የሚገኙ የግል ባንኮች ራሳቸውን ለውድድር እንዲያዘጋጁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አሳሰቡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በዚህ ወቅት በሰጡት ማብራሪያ የግል ባንኮች በዘርፉ እድገት ያስመዘገቡ ቢሆንም አሁንም ብዙ ስራዎች እንደሚጠብቃቸው ገልጸዋል፡፡


በተለይ እስካሁን የግል ባንኮች የውጭ ሀገራት የፋይናንስ ተቋማት ፈቃድ አለመሰጠቱ ለባንኮቹ እንደመልካም አጋጣሚ የሚቆጠር ቢሆንም ከእንግዲህ ግን በዚሁ መንገድ መቀጠል አይቻልም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስተሩ፡፡ በመሆኑም በሀገራችን የሚገኙ የግል ባንኮች ዘመናዊ አሰራርን በመዘርጋትና ፈጣን አገልግሎት ለደንበኞች በማቅረብ ብቁ ተወዳዳሪ ሆነው ለመቅረብ ከወዲሁ እንዲዘጋጁ አሳስበዋል፡፡


መንግስት የፖሊሲ ማሻሻያ ለማድረግ ዝግጅቱን የጀመረ በመሆኑ የውጭ ሀገራት ባንኮች ተፈቅዶላቸው በሀገራችን ስራ የሚጀምሩበት ጊዜ እሩቅ ላይሆን ይችላል ሲሉም አብራርተዋል፡፡ ጠቅላ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው የዚህ አይነቱ አሰራር ከጎረቤቶቻችን ጀምሮ በሌሎች ሀገራት የተለመደ አሰራር በመሆኑ ኢትዮጵያም ይህንኑ የአሰራር መንገድ ትከተላለች ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *