2 ሺህ 574 አመራሮችን ከሃላፊነት አንስቼያለሁ- ብልጽግና ፓርቲ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2014 ብልጽግና ፓርቲ በቅድመ ጉባኤ ግምገማ 2 ሺህ 574 አመራሮች ከሃላፊነት እንዲነሱ አድርጌያለሁ አለ
ፓርቲው ይህን ያለው የመጀመሪያ ጉባኤ መካሄዱን ተከትሎ ከቅድመ ጉባኤ እስከ ፍፃሜው ድረስ
የነበረውን ክንውን በማስመልከት መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው፡፡
የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ በፓርቲው ቅድመ ጉባኤ ግምገማ 108 ሺህ 258
አመራሮች ተገምግመው በ10 ሺህ 658 አመራሮች ላይ የተለያየ ደረጃ ያለው እርምጃ ተወስዷል
ብለዋል።
በፓርቲው እርምጃ ከተወሰደባቸው 10 ሺህ 658 መካከል 2 ሺህ 574 ከሃላፊነት እንዲነሱ
መደረጉንም ተናግረዋለ።
በቀሪዎቹ ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል ማስጠንቀቂያ፣ ከደረጃ ዝቅ ማድረግና የቦታ ሽግሽግ መደረጉን
ምክትል ፕሬዚዳነቱ ገልጸዋል።
የሙያ ስነ ምግባር፣ የአገልግሎት ስብዕና፣ የስራ ውጤታማነትና ሌሎችም የብቃት መለኪያዎች
አመራሮቹ የተገመገሙባቸው መስፈርቶች መሆናቸውንም አስታውሰዋል።
በጉባኤውም ፓርቲው በህዝቡ የተጣለበትን ሃላፊነት በብቃት ለመወጣት የሚያስችል ግምገማ ተደርጎ
ወሳኔ ተላልፏል ብለዋል።
ከልማት ፕሮጀክቶች አፈፃፀም አንፃር የነበረው ውስንነት ተገምግሞ በጥራት፣ በፍጥነትና ባልተጋነነ
ወጪ እንዲከናወኑ ማድረግ የሚያስችል አቅጣጫ መቀመጡንም ገልጸዋል።