loading
መንግሥት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9 ፣ 2014 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ እየተሳተፉ ከሚገኙ እና ለመሳተፍ ፍላጎት ካላቸው የህንድ ባለሀብቶች እና ከህንድ የኢንቨስትመንት ፎረም አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡ አምባሳደር ሬድዋን ኢትዮጵያ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከአሁን በፊት ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ያልሆኑ የኢንቨስትመንት ዘርፎችን ጭምር ክፍት ማድረጓን አስታውሰዋል።


የሕንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ወቅትም መዋለ ንዋያቸውን በማፍሰስ ሌሎች ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ መልካም አብነት ያላቸው ናቸው ብለዋል። ከባለሀብቶቹ ለተነሱት ጥያቄዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት እንደ ሀገር ለሁሉም ባለሀብቶች ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ እንዲፈጠር ይሰራል ነው ያሉት።
የህንድ ባለሀብቶች ኢትዮጵያ በዘርፉ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በፍጥነት መፍታት ከቻለች በአፍሪካ ቀንድ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ አህጉር ትልቋ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መዳረሻ የመሆን አቅም አላት ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ከባለሀብቶች የሚነሱ ጥያቄዎችን ጊዜ ሰጥቶ በማዳመጥ ለችግሮች እልባት
ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት ከውይይቱ በመረዳታችን ደስተኞች ነንም ብለዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *