የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዑስማን ሳልህ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ።
የኤርትሪያን ፕሬስ እንደዘገበዉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በቆይታቸው ከኢፌዴሪ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጉብኝቱ ዳግም የተጀመረውን የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ እንደሚያግዝም ታምኖበታል።
ኢትዮጵያና ኤርትራ ለ20 አመታት አቋርጠውት የነበረውን ግንኙነት ዳግም መጀመራቸው ይታወሳል።
በቅርቡም የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ወደ ኤርትራ በማቅናት ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው የሚታወስ ነው።