loading
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በሃገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋለው የመንጋ ፍትህ እና አላስፈላጊ ሁከት ተቀባይነት የሌለው እና የህግ የበላይነትን አደጋ ውስጥ የሚጥል መሆኑን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በ11ኛው እነ 12ኛው ዙር የሰለጠኑ የመከላከያ መኮንኖችን ባስመረቁበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ነው።

በወቅቱ ባደረጉት ንግግር ድርጊቱ የህግ የበላይነትን የሚነድ በመሆኑ በአስቸካይ ሊቆም እንደሚገባው ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ በተለይም ወጣቱ የተሳሳተ መረጃን መሰረት በማድረግ ለህግ ቅድሚያ ሳይሰጥ የሚፈጽማቸው ድርጊቶች እየተገነባች ያለችን ሃገር ከማፍረስ ውጭ ዋጋ እንደሌለውም ጠቅሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ የህግ የበላይነት ለአንድ ሀገር ማህበረሰብ መጠበቅ መሠረት መሆኑንም በዚህ ወቅት ተናግረዋል።

ከዚህ አንጻርም መንግስት አሁን ላይ እየተስተዋለ ያለውን ከህግ በላይ የመሆን ዝንባሌ እንደማይታገስም አንስተዋል።

“እንደመር ስንል ባለፍንበት መንገድ ያጣነውን ለመመለስ እንጅ ሃገሪቱን ውጤቱ ለከፋ ቀውስ ለመዳረግ አይደለምም” ብለዋል በንግግራቸው።

መንግስትም እነዚህን ክስተቶች ለመቆጣጠር የመከላከል እና ህግ የማስከበር ስራዎችን ይሰራልም ነው ያሉት።

(ኤፍ ቢ ሲ)

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *