loading
ሁለቱ ኮሪያዎች ድንበሩን አፍርሰው ድልድዩን መገንባት ጀመሩ

አርትስ 13/03/2011

ሰሜን ኮሪያ የወሰደችው እርምጃ ለሰላም ፈላጊው ሙን ጃይ ኢን የምስራች ነው፡፡

ፒዮንግያንግ በሁለቱ ጎረቤታሞች መካከል ፍቅር እንጂ ወታደራዊ ሀይል ሰላም አያሰፍንም በሚል እምነት የድንበር ጥበቃ ጣቢያዎችን ማፍረስ ጀምራለች፡፡

ሲ ጂ ቲ ኤን እንደዘገበው ሰሜን ኮሪያ እስካሁን ከደቡብ ጎረቤቷ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ለዓመታት ስትገለገልባቸው የነበሩ 10 የጥበቃ ማማዎችን  አፍርሳለች፡፡

ይህም በሁለቱ ሀገራት ድንበር አካባቢ ለዘመናት የዘለቀውን ውጥረት  የማርገብ ሀይል አንዳለው ተነግሮለታል፡፡

ይህ እርምጃ ፕሬዝዳንት ሙን ጃይ ኢን እና የሰሜን ኮሪያው አቻችው ኪም ጆንግ ኡን ባለፈው መስከረም ፒዮንግያንግ ላይ  ያደረጉት ስምምነት አካል ነው ተብሏል፡፡

ፕሬዝዳንት ሙን ጃይ ኢን በቀጠናው ሰላም እንዲሰፍን ያደረጉት ጥረት በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አስገግኝቶላቸዋል፡፡

ሙን ሁለቱ ኮሪያዎች ወደ ቀድሞ አንድነታቸው እንዲመለሱ ካላቸው ፍላጎት የተነሳ የውህደት ሚኒስትር እስከማቋቋም  ደርሰዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *