loading
ሁሉንም መራጭ ተደራሽ ለማድረግ የመራጮች ምዝገባ መራዘሙ እንደማየቀር ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2013 ሁሉንም መራጭ ተደራሽ ለማድረግ የመራጮች ምዝገባ መራዘሙ እንደማየቀር ተገለፀ፡፡ ይህ የተገለፀዉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ከሁለቱ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ በተወያዩበት ወቅት ነዉ፡፡

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢብርቱካን ሚዴቅሳ የመራጮች ምዝገባው ባለፉት ቀናት በተሻለ መንገድ እየተከናወነ መሆኑን በውይይቱ ላይ ጠቅሰዋል፡፡
ሆኖም ምዝገባው በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ሊጠናቀቅ አንድ ቀን ብቻ በመቅረቱ ሁሉንም መራጭ ተደራሽ ለማድረግ መራዘሙ የማይቀር ነው ብለዋል፡፡
ቦርዱ እስከመቼ እንደሚራዘም እንደሚውስን ይጠበቃል፡፡አሁን ባለው ሂደት ሲዳማ ክልል 80 በመቶ፣ አማራ 51 በመቶ፣ ኦሮሚያ 85 በመቶ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ 70 በመቶ፣ሐረሪ 55 በመቶ፣ ደቡብ 53 በመቶ፣ አዲስ አበባ 88 በመቶ፣ ድሬዳዋ 84፣ ሶማሌ 43 በመቶ በተከፈቱ የምርጫ ጣቢያዎች መራጮች መመዝገባቸው ተገልጿል፡፡

በአፋር ክልል ከ453 ሺህ በላይ ሰዎች የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸው ተገልጿል፡፡በዉይየቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዜጎች ሕገ-መንግስታዊ መብታቸውን ለመጠቀም በተቀረው ጊዜ ውስጥ ለመራጭነት የሚያበቃቸውን ካርድ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በኢትዮጵያም ስልጣን መያዣ መንገድ ዴሞክራሲያዊ እና ሰላማዊ የምርጫ ስልት ብቻ መሆኑን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ መግለጻቸዉን ፋና ዘግቧል

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *