loading
ህንድ ባጋጠማት የጎርፍ አደጋ የሟቾችና የተፈናቃዮች ቁጥር ጨምሯል፡፡

ህንድ ባጋጠማት የጎርፍ አደጋ የሟቾችና የተፈናቃዮች ቁጥር ጨምሯል፡፡
በክፍለ ዘመኑ አስከፊ የተባለለት ጎየርፍ አደጋ ያጋጠማት ህንድ 350 ዜጎቿ ለህልፈት ሲዳረጉ ከ800 ሽህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተፈናቅለዋል፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው ኬራላ በተባለችው የደቡባዊ ህንድ ግዛት የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ህይዎታቸው አደጋ ላይ ያሉ ዜጎችን ለመታደግ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አሁንም ጥረታቸውን ቀጥለዋል፡፡
በግዛቷ የሚገኙ ከ500 በላይ የሚሆኑ ዓሳ አስጋሪዎች ጀልባዎቻቸውን ይዘው ከአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጎን በመሰለፍ የወገኖቻቸውን ነፍስ ለመታደግ ደፋ ቀና ሲሉም ተስተውለዋል፡፡
የኬራላ ግዛት ባስልጣናት እንዳሉት በወዳጅ ዘመድ ቤት የተጠጉትን ጨምሮ የተፈናቀሉት ሰዎች ብዛት ከ1.5 ሚሊዮን ሊበልጥ ይችላል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *