loading
ህዳሴው ግድብ ላይ የሚደረገው ድርድርድር ከቴክኒክ አንፃር መሰረታዊ የተባሉ ጉዳዮች ቢፈቱም ሙሉ ስምምነት ሆኖ ለመውጣት የሚቀረው ጉዳይ እንዳለ ተገለፀ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11 ፣ 2012 ህዳሴው ግድብ ላይ የሚደረገው ድርድርድር ከቴክኒክ አንፃር መሰረታዊ የተባሉ ጉዳዮች ቢፈቱም ሙሉ ስምምነት ሆኖ ለመውጣት የሚቀረው ጉዳይ እንዳለ ተገለፀ:: በመጀመርያ የውሃ ሙሌትና አመታዊ ስራ ላይ ትኩረቱን አድርጎ በኢትዮጵያ በሱዳንና ግብፅ መካከል በቪዲዮ በመታገዝ እየተካሄደ ያለው ድርድር ለሰባተኛ ቀን ትላንት ተካሂዷል።የኢፌዴሪ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር እንዳለው ከሚኒስትሮቹ ውይይት ቀደም ብለው የሀገራቱ የቴክኒክና የህግ ቡድኖች በተናጥል በመነጋገር የደረሱበትን ሪፖርት አድርገዋል።ከቴክኒክ አንፃር መሰረታዊ የተባሉ ጉዳዮች በድርድር መፈታታቸውን ሚኒስቴሩ በመግለጫው አስታውቋል።ሆኖም ሙሉ ስምምነት ሆኖ ለመውጣት ግን ከህግ አንፃር ያሉት ጉዳዮች መፈታት እንዳለባቸው ነው የገለፀው ።

የሱዳን ተዳረዳሪዎች እሰካሁን በድርድሩ የተገኙ ውጤቶችን ለጠቅላይ ሚንስትራችን ማሳወቅና ተመካክረን መምጣት አለብን በማለታቸው እነርሱ ተመካክረው ሲመጡ ድረድሩን ለመቀጠል ከመግባባት ላይ መደረሱንም እስታውቋል።ሚኒስቴሩ በመግለጫው ብድርድሩ የህዳሴ ግድብ ስራውን ፍፁም በሆነ መልኩ እንዲያከናውን ከሚያስችል ስምምነት ከመድረስ ባለፈ ኢትያጵያ በአባይ ውሃ ላይ ቋሚ የሆነ የመጠቀም መብቷን እንዲረጋገጥ እንደሚሰራ ጠቁሟል። በተመሳሳይም የሱዳን እና ግብፅ መንግስታት የሁሉንም ሀገር ሉዓላዊነት እና የጋራ ተጠቃነትን የሚያረጋግጥ ዘላቂ ትብብር የሚፈጥርን መንገድ ሊይዙ እንደሚገባ አመልክቷል። ከ ኢቢሲ እንዳገኘነው መረጃ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት በተደረሰው የመርህዎች ስምምነት መሰረት አሁንም ግድቡን ውሃ የመሙላት መብት እንዳላት አስታውቋል ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *