loading
ሊቢያዊው አክቲቪስትና ፖለቲከኛ የጣሊያንን ጥረት አደነቁ

አርትስ አፍሪካ 05/03/2011

የሊቢያ የፍትህ እና ልማት ፓርቲ መሪ የሆኑት ሞሀመድ ሶዋን ጠሊያን የሊቢያ ተቃዋሚ ሀይሎችን ለማስማማት የምታደርገውን የሰላም ጥረት አመከሽተውታል፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ሶዋን ጣሊያን ያዘጋጀችው የፓርሌሞ ኮንፈረንስ ሀገሪቱ የገጠማትን ቀውስ ለመፍታት ሁነኛ የመግባበቢያ መድረክ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ምን እንኳን የኮንፈረንሱ ውጤት ገና በውል ያልታወቀ ቢሆንም በሊቢያ ያለውን በዘር፣ በአካባ፣ እና በሀይማኖት መከፋፈልን ግጭት በምክክር ለመፍታት የተጀመረወ ረት በራሱ እንድ እምጃ ነው ብለዋል፡፡

በሊቢያ ሰላምና መረጋጋትን  ለማምጣት በፖለቲካ የተከፋፈሉት ሀይሎች መወያየት ብቸኛው አማራጭ መሆኑን የተገነዘበው የተባበሩት መንግስታትም ምስጋና ይገባዋል ነው ያሉት ሶዋን፡፡

 በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሊቢያ ልዩ ልኡክ ጋሳን ሳላሜ ሁለቱ ወገኖች ተግባብተው ቀጣዩ ምርጫ በሰላም እንዲከናወን ደጋግመው መሳሰባቸው ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *