ልብን ለማዳን የልበ ቀናዎች የዘወትር ትጋት ያስፈልጋል…
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3፣ 2013 ማህበራዊ ድረ ገፅን ለበጎ አላማ በማዋል ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል አንድ ሚሊዮን ብር ተሰበሰበ፡፡ ማህበራዊ ድረ ገፅን ለበጎ አላማ የማዋል ዓላማ ይዛ በመነሳት የገንዘብ ድጋፉን ያሰባሰበችው ነዋሪነቷን በአሜሪካ ሀገር ያደረገች ህይወት ታደሰ የተበለች ጋዜጠኛ ናት፡፡
የማዕከሉ የበጎ ፍቃድ አምባሳደር አርቲስት መሰረት መብራቴ በርክክቡ ወቅት በተለይም ማህበራዊ ሚድያን ለፀብና ለቂም በቀል ከመጠቀም ባለፈ ለበጎ አለማ ማዋል ፋይዳው የጎላ ነው ብላላች ፡፡ በማዕከሉ ህክመና ለማግኝት ብዙ ሺህ ህፃናት ወረፋ እየጠበቁ መሆናቸውን የገለፁት የማዕከሉ ስራ አስኪያጅ ህሩያ አሊ እንድሪስ ሁሉም አቅሙ በፈቀደው ሁሉ ማዕከሉን እንዲደግፍ ጠይቀዋል፡፡ ማዕከሉ ከጨቅላ ህፃናት ጀምሮ በዕድሜ የገፉ ህሙማንን በአቅም ውስንነት ምክንያት በሳምንት ለ3 ቀናት ብቻ ህክምና እንየሰጠ እንደሚገኝ ነው የተነገረው::
ማዕከሉ ከህክምና መሳሪያ መለዋወጫ እጥረት ጋር በተያያዘ በተፈለገው ልክ አገልግሎት መስጠት አለመቻሉ የተገለጸ ሲሆን መላው ህዝብ በ67 10 A አጭር የፅሁፍ መልዕክት በመላክ በማዕከሉ ህክምና ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ህፃናትን መታደግ እንደሚገባ ተመለልክቷል፡፡በዶክተር በላይ አበጋዝ እና በጥቂት ልበ ቀና ኢትዮጵያውያን የተቋቋመው የኢትዮጵያ የልብ ሁሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል ለታካሚዎች ነፃ አገልግት እየሰጠ ይገኛል፡፡