loading
ሕገ ወጥ ግብይት ለምግብ ደኅንነት ችግር ቀዳሚ መንስኤ ነው-ኢንስቲትዩቱ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 1፣ 2013 ሕገ ወጥ ግብይት ለምግብ ደኅንነት ችግር ቀዳሚ መንስኤ ነው-ኢንስቲትዩቱ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከ40 በመቶ በላይ ሕጻናት የምግብ ደኅንነት ችግር እንደሚገጥማቸው ገለጸ፡፡በኢንስቲትዩቱ የምግብ ሳይንስ እና የስነ-ምግብ ምርምር ዳሬክተር ዶክተር ማስረሻ ተሰማ
በምግብ ደኅንነት ዙሪያ በርካታ ችግሮች እንደሚስተዋሉ ነው የገለጹት፡፡ ዳይሬክተሩ ከ40 በመቶ በላይ ሕጻናት ከምግብ ደኅንነት ችግር ጋር በተየያዘ ምክንያት ለመቀንጨር ችግር እንደሚጋለጡ ጠቅሰዋል፡፡

ዶክተር ማስረሻ አያይዘውም የምግብ ደኅንነት ችግር በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያደረሰ መሆኑን ነው የተናገሩት፡ ሕጋዊ ያልሆነ ግብይት በዋናነት በኢትዮጵያ ከምግብ ደኅንነት ችግር ጋር ተያይዘው ለሚነሱ ችግሮች መንስዔ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሠራበት እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡ ከምግብ ደኅንነት ጋር ተያይዘው የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በ24 ከተሞች በተደረገ ቅኝት የሚያስፈልጉ የገንዘብ ድጋፎችን በማድረግ በመሥራት ላይ እንደሚገኙም ዶክተር ማስረሻ ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር ወይዘሪት ሄራን ገርባ የምግብ ደኅንነት የሁሉም አካል ሀላፊነት መሆኑን በመገንዘብ ለተግባራዊነቱ በጋራ መሥራት ይገባል ብለዋል፡፡ የጤና ሚኒስተር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ በበኩላቸው ምግብ ደህንነቱ የተጠበቀ ከሆነ ለመጪው ትውልድ ትርጉም ያለው በመሆኑ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማስቀረት የቁጥጥር ስራ ላይ መሰራት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡ የሕግ አካላት፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በምግብ ደኅንነት የቁጥጥር ስራ ላይ ትልቅ ሚና ስላላቸው ተሳትፏቸውን ከፍ ማድረግ ያስፈልጋል መባሉን ከኢንስቲትዩቱ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *