ሚዲያዎች በሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ላይ በርትተው እንዲሰሩ ተጠየቀ
አርትስ 14/03/2011
የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ከኮሚኒኬሽንና ሚዲያ ተቋማት ጋር ሀገር አቀፍ መድረክ ያዘጋጀ ሲሆን የሚኒስቴሩ ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትርዴኤታ ወ/ሮ አለሚቱ ኦሞድ የመድረኩ ዓላማ የህፃናት፣ ሴቶችና ወጣቶችን መብቶች ማክበር፤ የህፃናት ደህንነትን ለማስከበር፤ ፍትሐዊተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ፤ የስራ ዕድል ፈጠራ እና ስብዕና ግንባታ ላይ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችንና መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽለማድረግ የሚያስችል የጋራ መግባባት ከሚዲያዎች ጋር ለመድረስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በሚኒስቴሩ የሴቶች ዘርፍ መኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ፤ በህፃናት፣ ሴቶችና ወጣቶች ላይ የሚሰሩ ስራዎች በተሻለ ሚዲያዎች ቢታገዙስኬቱ ትልቅ በመሆኑ ግንኙነቱ ሊያድግ ይገባል ብለዋል፡፡
በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመመከት የሚዲያ ተሳትፎ አሁን ካለው ከፍ ሊል ይገባል ያሉት ወ/ሮ ስመኝ፤ ከህዳር 16 ጀምሮ ለሁለትሳምንታት አለም አቀፍ የፀረ ፆታ ቀን ይከበራል፤ በዚህም ብዙ እንቅስቃሴዎች ይከናወኑበታል ሲሉ አክለዋል፡፡
በመድረኩ ሴቶች በሚዲያዎች የሚሰጣቸው ቦታ እና የሚሳሉበት መንገድ አግባብ እንዳልሆነ ተጠቅሷል፡፡ በሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ከመገናኛብዙሀን ጋር ስለነበራቸው ሚና እና ወደፊት ስለሚኖራቸው ቅርበት የተለያዩ ጥናቶች እየቀረቡ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ ለውጥ እንዲመጣከተፈለገም የሁሉም ህብረተሰብ አበርክቶና አስተሳሰብ ከፍ ሊል ይገባል ተብሏል፡፡