loading
ማኅበረሰቡ የኮሮናቫይረስ የመከላከያ መንገዶችን እንዲተገብር የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሳበ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6 ፣ 2013 ማኅበረሰቡ የኮሮናቫይረስ የመከላከያ መንገዶችን እንዲተገብር የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሳበ፡፡
ኢንስቲትዩቱ በህንድ የተከሰተው አዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያ አሳሳቢ እየኾነ መምጣቱን በማስታወስ ማህበረሰቡ እንዳይዘናጋ አስጠንቅቋል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት በህንድ የተከሰተው የኮሮናቫይረስ ዝርያ ዓለም አቀፍ ስጋት እየሆነ እንደመጣ መግለጹን ኢኒስቲትዩቱ አስታውቋል፡፡

ቫይረሱ እስካሁን በ44 ሀገራት እንደተሰራጨ መገለጹን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አመላክቷል፡፡ ቫይረሱ አሁንም የጤና ስጋት በመሆኑ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል የመከላከያ መንገዶችን በጥንቃቄ እንዲተገብር ነው የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያሳሰበው፡፡ በየቀኑ በከፐረፖናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ መመጣቱን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በየጊዜው የሚያወጣው ሪፖርት ያለክታል፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ምርመራ ከተደረገላቸው 5 ሽህ 621 ሰዎች መካከል 593 የሚሆኑት ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ሚኒስቴሩ ይፋ አድርጓል፡፡
ይህም በኢትዮጵያ በጠቅላላው በቫይረሱ የተያዙትን ሰዎች ቁጥር ወደ 264 ሺህ 960 ከፍ እንዲል አድርጎታል ነው የተባለው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *