loading
ማይክ ፖምፒዮ በመካከለኛው ምስራቅ የሚያደርጉትን ጉብኝት ጀመሩ፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 18፣ 2012 ማይክ ፖምፒዮ በመካከለኛው ምስራቅ የሚያደርጉትን ጉብኝት ጀመሩ፡፡በእየሩሳሌም ከእስራኤሉ አቻቸው ጋር የተገኙት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በተባበሩት አረብ ኤሜሬት ፣ በባህሬንና በሱዳን ጉብኝት እንደሚያደርጉም ይጠበቀል፡፡ፖምፒዮ በመካከለኛው ምስራቅ ለአምስት ቀናት የሚያደርጉትን ጉብኝት ከእስራኤል የጀመሩ ሲሆን ጉብኝቱም በእስራኤልና አረብ ሀገራት መከካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል ያለመ ነው ተብሏል፡፡

እንደ አልጄዚራ ዘገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በሱዳን፣ ባህሬንና በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ በተከታታይ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡የዋሽንግተን ጠንካራ አጋር የሆነቸው እስራኤል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢራንን ጨምሮ ከቀጠናው ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል ከፍተኛ ፍላጎት ማሳደሯ ነው የተነገረው ፡፡የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስርት ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ከፖምፒዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ሰላም ለማስፈን በቀጠናው ካሉ ሀገራት ጋር መስራት እንፈልጋለን ይህን ሀሰባችንን የሚጋሩ ሌሎች ሀገራት እንደሚኖሩም ባለሙሉ ተስፋ ነኝ ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *