loading
ምክር ቤቱ ዛሬ  መደበኛ ስብሰባውን ጀምሯል

ምክር ቤቱ ዛሬ  መደበኛ ስብሰባውን ጀምሯል

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን፣ 24ኛ መደበኛ ስብሰባ  ተጀምሮል፡፡

በምክርቤቱ ስብሰባ የምክርቤቱን 4ኛ አመት የስራ ዘመን 23ኛ መደበኛ እና 2ኛ ልዩ ስብሰባ ቃለ ጉባኤዎች መርምሮ ማጽደቅ፣

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የ2011 በጀት ዓመት የ6 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ማዳመጥ፣ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ለመሾም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ያጸድቃል፡፡

በተጨማሪም የዕርቀ-ሰላም ኮሚሽን አባላትን ለመሾም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ማጽደቅ እና  የሴቶች፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ፤የምግብና መድኃኒት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን ማጽደቅ እንዲሁም የህግ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን ፡ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *