ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 የስኳር ልማት ፕሮጀክትን ጎበኙ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 የስኳር ልማት ፕሮጀክትን ጎበኙ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በደቡብ ክልል በቤንች ማጂ ዞን የሚገኘውን የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 የስኳር ልማት ፕሮጀክት በትናንትናው ዕለት ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ወቅትም የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 የስኳር ልማት ፕሮጀክት በሙሉ አቅም የማምረት ሽግግር ሂደት ውጤታማ መሆኑን የፕሮጀክቱ የስራ ሃላፊዎች ገለፃ አድርገውላቸዋል።
በዚህ መሰረትም የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 የስኳር ልማት ፕሮጀክት በቀን 12 ሺህ ኩንታል ስኳር የማምረት ብቃት ላይ መድረሱ ነው የተገለፀው።
ፕሮጀክቱ በሙሉ አቅም የስኳር ምርት ደረጃ ላይ መድረሱን ያደነቁት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ ለፕሮጀክቱ ዘላቂ ውጤታማነት ባለሙያዎች በተሻለ ጥረት እንዲሰሩ አሳስበዋል።
በጉብኝቱም ከጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በተጨማሪ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች መሳተፋቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ስር ከሚገነቡት አራት ስኳር ፋብሪካዎች አንዱ ነው፡፡
በ8 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው ይህ የስኳር ፋብሪካ ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ በተገነኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ምንጭ ፦ፋና