ሞሮኮ የትራፊክ አደጋ ለዜጎቼ ህይዎት ስጋት ሆኖብኛል አለች፡፡
ሞሮኮ የትራፊክ አደጋ ለዜጎቼ ህይዎት ስጋት ሆኖብኛል አለች፡፡
በየዓመቱ በሽዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይዎታቸው እንደሚያልፍ እና በርካቶች ለከፋ የአካል ጉዳት እንደሚዳረጉ ነው የሀገሪቱ ባለስልጣናት የተናገሩት፡፡
ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው በሞሮኮ በየዓመቱ ከ3 ሺህ 600 በላይ ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሲሞቱ ቁጥራቸው 12 ሺህ የሚደርሱት ደግሞ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ይደርስባቸዋል፡፡
ይሄ ደግሞ በእያንዳንዱ ቀን በአማካይ በትራፊክ አደጋ 10 ሰው ሲሞት 52 ሰው የመቁሰል አደጋ ይደርስበታል ማለት ነው፡፡
ምክንያቱ ደግሞ በአብዛኛው በከፍተኛ ፍጥነት ከማሽከርከር ጋር የተገናኘ ሲሆን እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር 2018 ብቻ 1.4 ሚሊዮን የፍጥነት ወሰን መተላለፍ ክስተቶች አጋጥመዋል፡፡
ሞሮኮ በዚህ የተነሳ በየዓመቱ 2.5 በመቶ የሀገር ውስጥ ጥቅል ምርቷን የሚሸፍን የኢኮኖሚ ኪሳራ ይደርስባታል፡፡ ይሄም በገንዘብ ሲሰላ 1.5 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንደማለት ነው፡፡
የቅርብ ጊዜ የጥናት ትንበያዎች እንደሚያሳዩት በዓለማችን በየቀኑ የሚከሰተው የትራፊክ አደጋ በዚህ ከቀጠለ በፈረንጆቹ 2030 2.4 ሚሊዮን ሰዎች ከዚሁ ጋር በተያየዘ ህይዎታቸውን ሊያጡ ይችላ፡፡
መንገሻ ዓለሙ