ሞስኮ ወደ ክሬሚያ ድንበር ዘመናዊ ሚሳኤሎችን ልታጓጉዝ ነው
አርትስ 20/03/2011
ሩሲያ ከዩክሬን ጋር አሰጥ አገባ ውስጥ መግባቷን ተከትሎ ኤስ 400 በተሰኘው ዘመናዊ ሚሳኤል የተደራጀ ጦሯን ልታስጠጋ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
ሮይርተስ እደንደዘገበው ሩሲያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2014 ክሬሚያን ወደ ግዛቷ ካስገባች ጀምሮ በየጊዜው ዘመኑ ያፈራቸውን ሚሳኤሎችን በአካባቢው ማከማቸቱን ተያይዛዋለች፡፡
የሩሲያ ደቡባዊ ወታደራዊ እዝ ቃል አቀባይ ቫዲም አስታፊየቭ (Vadim Astafyev) እንዳስታወቁት ኤስ 400 የተባለውን ዘመናዊ ሚሳኤል የታጠቀው ሻለቃ ጦር በፍጥነት ወደ ክሬሚያ ተንቀሰሳቅሶ ለግዳጅ ዝግጁ ይሆናል፡፡
ሩሲያ ወታደራዊ ሀይሏን በክሬሚያ ማከማቸት የረዥም ጊዜ እቅዷ ቢሆም አሁን ለዩክሬን መልእክት በማስተላለፍ ትክክለኛው ጊዜ ሆኖላታል ተብሏል፡፡
ክሪሜያ ውስጥ እስከ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት በሚሸፍን ሚሳኤል ታግዘው ግዳጃቸውን መወጣት የሚችሉ አራት ሻለቃ የጦር ሰራዊት አባላት ጥቁር ባህርን በተጠንቀቅ እየጠበቁ መሆኑም ተገልጿል፡፡
የሩሲያ ክሪሜያ ሚሳኤሎችን ማስጠጋቷ ውጥረቱን ይበልጥ ያባብሰዋል በማለት የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ቅሬታውን አሰምቷል፡፡