loading
ረዳት አርቢትር ተመስገን ሳሙኤል በኒጀር ከ20 ዓመት በታች ውድድር በዳኝነት ይካፈላል ተባለ

ረዳት አርቢትር ተመስገን ሳሙኤል በኒጀር ከ20 ዓመት በታች ውድድር በዳኝነት ይካፈላል ተባለ

የቶታል ካፍ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ፤ በሀገር ውስጥ ውድድር እየተካፈሉ በሚገኙ ተጫዋቾች ብቻ የሚወዳደሩበት ውድድር በኒጀር እ.አ.አ ከየካቲት 2- 17 /2019 ይካሄዳል፡፡

ውድድሩን በዳኝነት እንዲመራ ከተመረጡ አርቢትሮች መካከል፤ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ተመስገን አታንጐ መመረጣቸውን የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን /ካፍ/ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላከው ዝርዝር መረጃ ገልጿል፡፡

ዳኛ ተመስገንን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት በረዳት ዳኝነት 12 እንዲሁም በዋና ዳኝነት 12 ዳኞች የተመረጡ ሲሆን ከውድድሩ በፊት ለባለሙያዎቹ የአካል ብቃት፣ የንድፈ ሃሳብና የሙያ ምዘና እንደሚደረግላቸው እና በብቃት መወጣት የቻሉ ዳኞች ብቻ ውድድሩን እንደሚመሩ ተገልጿል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *