loading
ሮሀኒ አሜሪካ የተሳሳተ መንገድ ስለመረጠች ትሸነፋለች አሉ

አርትስ 05/03/2011

ሮይተርስ እንደዘገበው የኢራኑ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሮሀኒ ዋሽንግተን በሀገራቸው ላይ የጣለችው ማእቀብ የሽንፈቷን ጊዜ እንደሚያፋጥነው ተናግረዋል፡፡

አሜሪካ የመረጠችው መንገድ ከዓለም አቀፉ ህግ ያፈነገጠ በመሆኑ መቸም ቢሆን አሸናፊ እንደማያደርጋት ልንነግራት አንፈልጋል በማለት ምክንያታቸውን አብራርተዋል፡፡

እውነት አሜሪካ እንደምትለው ለቀጠናው መረጋጋት ብትቆረቆር ይህን መንገድ አትመርጥም ነበር ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕና አስተዳደራቸው እውነተኛ እና ታማኝ ቢሆኑ ኖሮ ለኢራን ህዝብ ክብር ይኖራቸው ነበርም ብለዋል ፡፡

የአሜሪካ የደህንነት አማካሪ ጆን ቦልተን በኢራን ላይ የተጣለው ማእቀብ ተግባራዊ እንዲሆን እየሰራን ነው ቢሉም ሮሀኒ ግን ከሌሎች ወዳጆቻችን ጋር ሆነን የትኛውንም ተራራ እንወጣዋለን ብለዋል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *