ሱዳን በፀጥታ ችግር ምክንያት ትምህርት ቤቶቿን ዘጋች፡፡
ሱዳን በፀጥታ ችግር ምክንያት ትምህርት ቤቶቿን ዘጋች፡፡
ሰሞኑን በኮርዶፋን አካባቢ በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ ተማሪዎች መገደላቸው ሱዳናዊያንን አስቆጥቷል፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበው በመላ ሀገሪቱ የተቃውሞ ሰልፍ እንዲደረግ ከተቃዋሚዎች ጥሪ ተላልፏል፡፡
ውጥረቱ እየተባባሰ መምጣቱ ያሳሰበው የሱዳን ጊዜያዊ ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት የሰዓት እላፊ ገደብ ከመጣል ጀምሮ በሀገሪቱ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላልተወሰነ ጊዜ እንዲዘጉ ወስኗል፡፡
የሽግግር ምክር ቤቱ እና ተቃዋሚዎቹ ለሶስት ዓመት በስራ ላይ የሚቆይ የጋራ የሲቪል አስተዳደር ለመመስረት ወደ ስምምነት በተቃረቡበት ወቅት ይህ ችግር መፈጠሩ የነበረውን ተስፋ አጨልሞታል ተብሏል፡፡
መንገሻ ዓለሙ