loading
ስፔን የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ብሄራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና የሰዓት እላፊ ገደቦችን ደነገገች::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2013 ስፔን የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ብሄራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና የሰዓት እላፊ ገደቦችን ደነገገች::የስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቸዝ ለመነሻነት ለ15 ቀናት የተጣለው ድንጋጌ ለስድት ወራት እንዲራዘም ፓርላማቸዉን እንደሚጠይቁ ተናግረዋል፡፡በተለያዩ ግዛቶች የተጣሉት የምሽት ጊዜ የሰዓት እላፊ ገደቦች እንደአስፈላጊነቱ ሊያጥሩና ሊረዝሙ አንደሚችሉ ነው የተነገረው፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው አዲሱ የስፔን የእንቅስቃሴ እቀባ በግልም ሆነ በመንግስት በሚደረጉ መሰባሰቦች በአንድ ቦታ ከስድስት ሰዎች በላይ በአንድ ጊዜ እንዳይገኙ የሚገድብ ነው፡፡ስፔን ይህን እርምጃ ለመውሰድ የተገደደችው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዳግም አገርሽቶ ህዝቧን ስጋት ውስጥ ስለጣለባት ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት በመላው ዓለም እንደ አዲስ እየተስፋፋ ሲሆን በተለይ በአብዛኞቹ የአውሮፓ ሀገራት ሁኔታው መባባሱ ይነገራል፡፡ስፔን በመጀመሪያው ዙር በቫይረሱ ክፉኛ ተጠቅታ እንደነበርና በርካታ ዜጎቿ በበሽታው ሳቢያ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቸዝ ሁኔታውን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ በሽታውን በጊዜ ካልተቆጣጠርነው እንደ ከአሁን ቀደሙ ከባድ ዋጋ ያስከፍለናል ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *