loading
በሀገሪቱ 80 አዳዲስ የእጽዋት ክሊኒኮች ግንባታ ሊካሄድ ነው

በሀገሪቱ 80 አዳዲስ የእጽዋት ክሊኒኮች ግንባታ ሊካሄድ ነው

አርትስ 27/02/2011

 

ይህ የተባለው በሰብልና መስኖ ልማት ላይ የሚደርሰውን ችግር ከመከላከል አንፃር የእጽዋት ክሊኒኮች የነበራቸውን አስተዋጽኦ የሚገመግም መድረክ  በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡

በመድረኩ ላይ የግብርና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ተምች  እና የአፈር ውስጥ ባክቴሪያ በሰብል፣ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ላይ የሚያደርሰውን  ጉዳት አስቀድሞ ለመከላከል ዘንድሮ 80 የአዳዲስየእጽዋት ክሊኒክ ግንባታ ይከናወናል።

በሚኒስቴሩ የእጽዋት ጤናና ምርት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ወልደሃዋሪያት አሰፋ እንደገለጹት  ተምችን ጨምሮ ሌሎች በአፈር ውስጥ ያሉ ባክቴሪያዎች የግብርና ምርትና ምርታማነትን ከ20 እስከ25 በመቶ ይቀንሳሉ።

በዚህም በኦሮሚያ፣ ትግራይ፣አማራና ደቡብ ክልሎች ቀደም ሲል 107 ክሊኒኮች ተገንብተው ለአርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ማህበረሰብ ጥምር አገልግሎት እየሰጡ  ነው ተብሏል።

በተያዘው የበጀት ዓመትም በዘጠኙም ክልሎች 80 ተጨማሪ የእፅዋት ክሊኒኮችን ለመገንባት ዝግጅት መጠናቀቁም ተጠቁሟል እንደ ኢዜአ ዘገባ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *