loading
በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ ሊጀመር ነው::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 3፣ 2013 በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብርን ለመጀመር ጥናት እየተደረገ ነው::በአዲስ አበባ የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብርን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለማስጀመር ጥናት እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተማሪዎች ምግብ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ የኤጀንሲው ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ምህረት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ በ2014 በጀት ዓመት ለምገባ መርሃ ግብር 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዟል፡፡ ይህም ከአምናው ጋር ሲነፃጸር የ500 ሚሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል። ከአምናው በበለጠ የተማሪዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል የጠቀሱት አቶ ኢሳያስ የግብዓት አቅርቦትም ላይ ያለውን ዋጋ ታሳቢ ተደርጎ በጀቱ መያዙን ተናግረዋል።

ቀድሞ ምገባው ይካሄድ ከነበረው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተጨማሪም የምገባ መርሃ-ግብሩን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለማስጀመር ጥናት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡በተቋም ደረጃ በተደረገው ጥናት ምገባው በተማሪዎች ስነልቦና ላይ ጥሩ ውጤት አምጥቷል፡፡ በዚህም ከትምህርት ቤት መቅረት፣ማርፈድ እና የክፍል መውደቅ የመሳሰሉት ችግሮች እንደተቀረፈም ጠቅሰዋል፡፡ በሌላ በኩል ለደንብ ልብስ ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መያዙን የተናገሩት ዳይሬክተሩ በተለይም በሴቶች የንጽህና መጠበቂያና በመሳሰሉት ቁሳቁሶች ላይ ህብረተሰቡ የተለመደ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *