በሊቢያ በሚካሄደው ጦርነት ንፁሀን ሞት ቀጥሏል፡፡
በሊቢያ በሚካሄደው ጦርነት ንፁሀን ሞት ቀጥሏል፡፡
በሊቢያ ንግስት እና በተቃዋሚው ጄኔራል ሀፍታር ጦር መካከል በሚደረገው ውጊያ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡
አናዶሉ የዜና ወኪል ድርጅቱን ጠቅሶ እንደዘገበው እስካሁን በግጭቱ ምክንያት 254 ሰዎች ተገድለዋል፡፡
ከሟቹቹ በተጨማሪ ከ1 ሺህ 200 በላይ ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን ከ30 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ራሳቸውን ከአደጋ ለመጠበቅ ሲሉ ቀያቸውን ጥለው ተሰደዋል፡፡
ሊቢያ የቀድሞ መሪዋ ሞዓመር ጋዳፊ በምእራባዊያን መሪነት በሀይል ከስልጣን ከተወገዱ እና ከተደገሉ በኋላ በሁለት ሀይሎች ተከፍላ ባለመረጋጋት ውስጥ ትገኛለች፡፡
የትሪፖሊን መንግስት የተባበሩት መንግስታት ሲደግፈው የጄኔራል ከሊፋ ሀፍታር ጦር ደግሞ ከአሜሪካ እና አጋሮቿ አይዞህ መባሉ ይነገራል፡፡
መንገሻ ዓለሙ