loading
በመዲናዋ የአዳዲስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ተጧጡፈዋል

በመዲናዋ አዳዲስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ተጧጡፈዋል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 1.4 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 30 ሜትር ስፋት ያለውን የሽሮሜዳ ቁስቋም አስፓልት መንገድ እንዲሁም  ከ5 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመትና 25 ሜትር ስፋት ያለው የአቃቂ ቱሉ ዲምቱ የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክቶችን አስጀምሯል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊው ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ የመንገዶቹ ግንባታ በ2 አመት  ይጠናቀቃል ብለዋል፡፡

የፕሮጀክት ግንባታው ሲጠናቀቅም ከሚኖራቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ባሻገር የመዲናዋን ገፅታ እንደሚያሻሽሉ ሀላፊው አብራርተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት በገፁ እንዳሰፈረው  የከተማ አስተዳደሩ  ከነዚህ ፕሮጀክቶች በተጨማሪ ከ120 በላይ የመንገድ ፕሮጀክቶችን በራስ ኃይልና በተቋራጮች አማካኝነት በመገንባት ላይ  ላይ ነው፡፡

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *