loading
በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች ተከስቶ በነበረው ግጭት የተቃጠሉ ቤቶች መልሰው እየተሰሩ ነው።

በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች ተከስቶ በነበረው ግጭት የተቃጠሉ ቤቶች መልሰው እየተሰሩ ነው።

በአሁኑ ሰአት 6 ሺህ 652 ቤቶችን ለመገንባት ጥረት እየተደረገ ሲሆን፥ እስከአሁን ከ1 ሺህ በላይ ቤቶች ቆርቆሮ ለብሰዋል።

የአማራ ክልል አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ፕሮግራምና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አማረ ክንዴ እንደገለፁት፥ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምዕራብ ደምቢያ ወረዳ ጉንትር በተባለው ቀበሌ ብቻ ከሚገነቡት 507 ቤቶች 432ቱ ቆርቆሮ የማልበስ ስራ ተከናውኗል።

በዞኑ 36 ሺህ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው የተመለሱ መሆናቸውን የተናገሩት አቶ አማረ፥ በዘላቂነት ለማቋቋም ድጋፉ እንደቀጠለ ነው ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ጊዜያዊ ድጋፎች እየተደረጉ ሲሆን፥ ለአርሶ አደሩ የእርሻ ስራና ለክረምት ምግብ የሚሆን አቅርቦት ለማድረግም ዝግጅቱ ተጠናቋል።

በክልሉ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ ቃል ከተገባው 720 ሚሊየን ብር 318 ነጥብ 6 ሚሊየኑ ገቢ የተደረገ ሲሆን፥ ይህንን ገንዘብ በፍትሀዊነት ለታለመለት አላማ ለማዋል በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *