loading
በማይናማር ታስረው የነበሩ የሮይተርስ ጋዜጠኞች ተፈቱ፡፡

 

በማይናማር ታስረው የነበሩ የሮይተርስ ጋዜጠኞች ተፈቱ፡፡

ሁለቱ የሮይተርስ ጋዜጠኞች በማይናማር በሮሂንጊያ ሙስሊሞች ላይ የደረሰውን በደል በማጋለጣቸው ነበር ለእስር የተዳረጉት፡፡

ጋዜጠኞቹ ከቀናት በፊት በኢትዮጵያ በተከበረው የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀን ላይ በተወካያቸው አማከኝነት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

የ33 ዓመቱ ዋሎን እና የ29 ዓመቱ ኪያው ሶኤ ኦ ከእስር የተፈቱት የማይናማር ፕሬዝዳንት ባደረጉላቸው ይቅርታ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ጋዜጠኞቹ ከአምስት መቶ በላይ ቀናት ከማይናማር ዋና ከተማ ርቃ በምትገኘው ያንጎን ከተማ በእስር  መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

ጋዜጠኞቹ በሮሂንጊያ ሙስሊሞች ላይ የደረሰባቸውን በደል በማጋለጣቸው ጥፋተኛ ተብለው እያንዳንዳቸው የሰባት ዓመት እስር ተፈርዶባቸው ነበር፡፡

የሮይተርስ ጋዜጠኞቹ ለእስር መዳረግ  የሀገሪቱን የመገናኛ ብዙሃን ነጻነትን በእጅጉ ያስወቀሰና በአጠቃላይ  ዴሞክራሲውንም ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ነው፡፡

ጋዜጠኛ ዋሎን ከእስር እንደተለቀቀ ለቢቢሲ በሰጠው ቃል በጋዜጠኝነት ስራው የተናገረ ሲሆን ፤ ቤተሰቦቼና ባልደረቦቼ ናፍቀውኛል ወደ ዜና ክፍል እስከምገባ  ጓጉቻለሁ ብሏል፡፡

በማይናማር አዲስ ዓመት ሲከበር በየዓመቱ ለእስረኞች ይቅርታ የሚደረግ ሲሆን የጋዜጠኞቹ ከእስር መፈታትም ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው፡፡

የሮይተርስ ከፍተኛ ዋና አዘጋጅ ስለ ጋዜጠኞቹ ሲናገር የፕሬስ ነጻነት ተምሳሌት ብሏቸዋል፡፡

ጋዜጠኞቹ የማይናማር ዜግነት ያላቸው ሲሆን የሮይተርስ ዘጋቢ እንደነበሩም ይታወሳል፡፡

 

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *