loading
በማዳጋስካር ምርጫ አንድሪ ራጆሊና ድል ቀንቷቸዋል

በማዳጋስካር ምርጫ አንድሪ ራጆሊና ድል ቀንቷቸዋል

አሸናፊና ተሸናፊዎቹ ፕሬዝዳንቶች እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2009 በሚገባ ይተዋወቃሉ፡፡

የአሁኑን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ማሸነፍ ያቃታቸው ማርክ ራቫሎማናና ማዳጋስካርን በፕሬዝዳንትነት ይመሩ በነበረበት ወቅት የአሁኑ ባለድል አንድሪ ራጆሊና ደግሞ የአንታናናሪቮ ከንቲባ ነበሩ፡፡

የኋላ ኋላ ግን ራጆሊና ከመከላከያ ሀይሉ ጋር በማበር ራቫሎማናና ከስልጠን እንዲወርዱ የአንበሳውን ድርሻ ተወጥተዋል ነው የሚባለው ፡፡

ከዚያም ራጆሊና በፈረንጆቹ ከ2009 እስከ 2014 ማዳስካርን ከአሁኑ ተቀናቃኛቸው ማክ ራቫሎማናና ነጥቀው አስተዳድረዋል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው ራጆሊና ምርጫውን ያሸነፉት ከ55 በመቶ በላይ  በሆነ ድምፅ ነው፡፡ ተሸናፊው ራቫሎማናና ደግሞ የመራጮቻቸውን 44 በመቶ ድምፅ አግኝተዋል፡፡

የሀገሪቱ ከፍተኛ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ውጤቱን  ካሳወቀ በኋላ ተሸናፊው ተፎካካሪ የክስ አቤቱታቸውን ይዘው የፍትህ ያለህ ውጤቱ ተጭበርብሯል በማለት ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

አሸናፊው ፕዝዳንት አንድሪ ራጆሊና በበኩላቸው ፍርድ ቤቱ ድላቸውን ካበሰረላቸው በኋላ ይህ ውጤት የናንተ እንጂ የኔ አይደለም በማለት ደጋፊዎቻቸውን አመስግነዋል፡፡

ሁለቱ ተፎካካሪዎች ባለፈው ህዳር በስልጣን ላይ ካሉት ፕሬዝዳንት ጋር ሲወዳደሩ ከፍተኛውን ድምፅ ቢያገኙም ከ50 በመቶ በላይ  ድምፅ ባለማግኘታቸው ሀገሪቱ ሁለተኛ ዙር ምርጫ ለማድረግ ተገዳለች፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *