loading
በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን እናስቁም በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን እናስቁም! በሚል ነፃ የሰልክ መስመር ተዘጋጀ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 4 ፣ 2013 በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን እናስቁም በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን እናስቁም! በሚል ነፃ የሰልክ መስመር ተዘጋጀ:: የኢትዮጵያ ሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ከዩ ኤን ኤፍ ፒ ኤ እና ካናዳ ኢምባሲ ጋር በጋራ በመሆን የህግ ድጋፍ እና ማማከር አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎችም አገልግሎቶችን በዘላቂነት የሚሰጥ 7711 ነፃ የስልክ መስመር አስመረቀ፡፡

የኢትዮጵያ ሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ከዩ ኤስ ኤ አይ ዲ እና ናሽናል ዲሞክራቲክ ኢኒስቲቲዉሽን (ኤን ዲ አይ) ጋር በመተባበር በመጪዉ 6ኛዉ ሃገር-ዓቀፍ ምርጫ ሂደት ዉስጥ በሴቶቸ ላይ ጥቃቶች ከተፈፀሙ ጥቆማዎችን ለመቀበል ፣ የህግ ድጋፍ እና ማማከር አገልግሎቶች እንዲሁም ሌሎች መረጃዎችን ለመስጠት የሚያስችል ተጨማሪ አገልግሎት በቅድመ-ምርጫ ፣ በምርጫ እና ድሕረ-ምርጫ ወቅት ለመስጠት ሰፊ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ነው የገለፀው፡፡

7711 በነፃ ስልክ መስመር ላይ በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት በመደወል የህግ ድጋፍ እና ማማከር አገልግሎት ጨምሮ በአቅራቢያ ስለሚገኙ የሚመለከታቸዉ አካላት አገልግሎቶች መረጃ ማግኝት የሚችል መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ አገልግሎት በይፋ ለማስጀመርም ከአጋር ድርጅቱ ኤን ዲ አይ ፣ ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፣ ሰብዓዊ መብቶች ላይ ከሚሰሩ የሲቪክ ማሕበራት እና ተቋማት እንዲሁም ከሚዲያ አካላት ተወካዮች በተገኙበት በሒልተን ሆቴል የማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት አከናዉኗል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *