loading
በሱዳን ዳግም ግጭት ማገርሸት በምስራቃዊ ሱዳን ዳግም ባገረሸው ግጭት የ4 ሰዎች ህይዎት ማለፉ ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ4፣ 2012 በሱዳን ዳግም ግጭት ማገርሸት በምስራቃዊ ሱዳን ዳግም ባገረሸው ግጭት የ4 ሰዎች ህይዎት ማለፉ ተሰማ:: የዓይን እማኞችን ጠቅሶ ሱዳን ትሪቢዩን እንደዘገበው በፖርት ሱዳን አካባቢ የሚኖሩ የቤኒ አሚር ጎሳዎች የኑባ ጎሳዎች ላይ ጥቃት በማድረሳቸው ነው ግጭቱ የተቀሰቀሰው፡፡
ለአሁኑ ግጭት መንስኤ ናቸው የተባሉት የቤኒአሚር ጎሳዎች መሆናቸውን ያመለከተው ዘገባው ኑባዎቹ ለግዛት አስተዳዳሪያቸው ባዘጋጁት መታሰቢያ ላይ ተሰባስበው ጉዞ በሚያደርጉበት ወቅት በቤኒ አመሮቹ ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል ብሏለወ፡፡ ሁለቱ ጎሳዎች ካለፈው ዓመት ጀምሮ ተደጋጋሚ ግጭቶችን ያደረጉ

ሲሆን መንግስት በመሀል ገብቶ ለማስማማት ጥረት ቢያደርግም አልተሳካለትም ተብሏል፡፡ በግጭቱም አራት ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 34 የሚሆኑ ደግሞ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ነው የተባለው፡፡ ከቆሰሉት መካከል የሚበዙት አደገኛ ሁኔታ ላይ በመሆናቸው የሞት መጠኑ ከፍ ሊል እልደሚችል የጤና ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡ በሱዳን ዳርፉር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተቀሰቀሰ የጎሳ ግጭት ከ60 በላይ ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታ ድርጅት በሪፖርቱ ይፋ አድርጓል፡፡በቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ጊዜ በርካታ ጥቃቶች፣ ሞትና ስደት ሲያስተናግዱ የነበሩት ነዋሪዎች ዛሬም በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ዘመንም ችግሩ አብሯቸው ቀጥሏል ሲል የዘገበው ደግሞ አልጀዚራ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *