loading
በሶስት የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች 990 ሺህ ብር የሚጠጋ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

በሶስት የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች 990 ሺህ ብር የሚጠጋ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

የገቢዎች ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ግምታቸው 989,800 ብር የሆኑ ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት በአርበረከቴ ፣ በቶጎጫሌ እና  በሐረር የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች  ነው።

 

አርበረከቴ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በአህዮች ተጭኖ ሲጓጓዙ በቁጥጥር ስር የዋሉት ኮንትሮባንድ እቃዎች መድሃኒት፣ መነፅርና አልባሳት ሲሆኑ በቶጎጫሌ መቆጣጠሪያ ጣቢያ

ደግሞ የሠሌዳ ቁጥሩ 3-54157 ኦሮ ተሸከርካሪ መኪና ውስጥ ተደብቆ ከሃገር ሊወጣ ሲል የተያዘው  አርባ አንድ ማካሮቨ ጥይት ነው።

 

ሐረር የመቆጣጠሪያ ጣቢያ ውስጥ ደግሞ 160 ሺህ ብር የሆነ ምንጣፍ ፣የመኪና ጎማ፣ የምግብ ዘይት እና ስኳር ደግሞ የሠሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-49504 እና ኮድ 3-44558 ኦሮ በሆኑ ተሽከርካሪዎች ተጭኖ ሲንቀሣቀሥ በቁጥጥር ሰር የዋለ ነው ተብሏል።

 

የተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች በሙሉ ለመንግስት ገቢ መደረጋቸውም ተነግሯል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *