በቡራዩና በተለያዩ አካባቢዎች በተፈፀመ ጥቃት የተጠረጠሩ 89 ግለሰቦች ምርመራ ወደ ፌዴራል ተዛወረ
አርትስ 26/02/2011
በቡራዩ ከተማና አካባቢው ተከስቶበነበረው ሁከትና ብጥብጥ የተጠረጠሩ 89 ግለሰቦች ምርመራ ወደ ፌዴራል የሕግተቋማት መዛወሩ ተነግሯል፡፡
የወንጀል ድርጊቱ በተፈጸመባቸውአካባቢዎች በሚገኙ ፍርድ ቤቶችእየቀረቡና ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮእየተጠየቀባቸው ከአንድ ወር በላይ በእስርየቆዩት ተጠርጣሪዎች የምርመራ መዝገብ፣ወደ ፌዴራል ወንጀል ምርመራ ቢሮና ፍርድቤቶች የተቀየረው በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግትዕዛዝ መሆኑ ታውቋል፡፡
ሪፖርተር እንደዘገበው መርማሪ ቡድኑ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ክፍለ ከተሞችግድያ በመፈፀም የተጠረጠሩ 32 ግለሰቦችን ጨምሮ በአጠቃላይምርመራቸው በአዲስ አበባ ፖሊስ ተይዞየነበሩ 89 ተጠርጣሪዎች የምርመራ ሂደትናየወንጀሉ አፈጻጸም በፀረ ሽብርተኝነት ሕጉሥር የሚወድቅ በመሆኑ፣ ለተጨማሪምርመራ በአዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ(20) መሠረት 28 ቀናት እንዲፈቀድለትፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው የተጠየቀባቸውን ተጨማሪ ጊዜተቃውመው ተጠርጣሪዎች ከታሰሩ ከአንድወር በላይ እንደሆናቸው፣ ከስድስት ጊዜበላይ ፍርድ ቤት ሲመላለሱ መክረማቸውንናምርመራው ተጣርቶ ያለቀ በመሆኑ ሊለቀቁእንጂ ወደ ሌላ የምርመራ አካል ተሸጋግረውተጨማሪ ጊዜ ሊጠየቅባቸው እንደማይገባተናግረዋል፡፡