በቻይና 132 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበር ቦይንግ 737 አውፕላን መከስከሱ ተሰማ፡፡
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 በቻይና 132 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበር ቦይንግ 737 አውፕላን መከስከሱ ተሰማ፡፡ የምስራቅ ቻይና አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላኑ ጉዋንግዚ በተባለች ግዛት የተከሰከሰ ሲሆን የአደጋው መንስኤ እተጣራ ነው ተብሏል፡፡ አደጋው የተከሰተው አውሮፕላኑ መንገደኞችን ከኩሚንግ ወደ ጉዋንግዙ ከተማ በሚያጓጓጉዝበት ወቅት መሆኑን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡
አልጀዚራ ከቻይና ባሰራጨው ዘገባ ሀገሪቱ በዓመት ውስጥ ያጋጠማት ትልቁ የአቬዬሽን አደጋ መሆኑን በመጥቀስ አስነብቧል፡፡ አደጋው በተከሰተበት ስፍራ በርካታ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የተሰማሩ ሲሆን ይህ ዘገባ እስተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ተሳፋሪዎች በህይዎት ይትረፉ አይትረፉ አልታወቀም፡፡ አውሮፕላኑ በወደቀበት አካባቢ እሳት መነሳቱን የሚያሳዩ ምልክቶች መኖራቸውን የገለጸው አልጀዚራ ከከተማ ውጭ በተራራማ ስፍራ መሆኑ ጋር ተዳምሮ ለአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ሁኔታውን አስቸጋሪ
እንደሚያደርገው አብረርቷል፡፡ ቻይና የከፋ የአውሮፕላን አደጋ የገጠማት እንደአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2010 ሲሆን በዚህ አደጋ ሳቢያ ከ96 ተሳፋሪዎች መካከል 44 ያህሉ መሞታቸው ይታወሳል፡፡