loading
በአራተኛ ዙር 274 ዜጎች ከኩዌት ወደ አገራቸው መሸኘታቸዉን በኩዌት የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2012 በአራተኛ ዙር 274 ዜጎች ከኩዌት ወደ አገራቸው መሸኘታቸዉን በኩዌት የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡ የኩዌት መንግሥት ያወጣውን የምህረት አዋጅ በመጠቀም ከኩዌት ወደ አገራቸው ለመመለስ ሲጠባበቁ የነበሩ 274 ዜጎች በአራተኛው ዙር ሰኔ 8 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ አገራቸው ተሸኝተዋል።ዜጎቻችን በኩዌት ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በአምባሳደር አብዱልፈታህ አብዱላሂ፣ ዲፕሎማቶችና ሰራተኞች እንዲሁም በኮሚኒቲ አመራሮች ሽኝት ተደርጎላቸዋል።እስካሁን በተደረገው ዜጎችን ወደ አገር የመመለስ ሥራ በችግር ምክንያት በመጠለያ የነበሩ 1ሺህ 23 ዜጎች ከኩዌት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል። ከእነዚህም መካከል 8 ህጻናት ይገኙበታል።

ምንጭ፤- በኩዌት የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *