loading
በአዲስ አበባ ድጋፍ ሰጪ አውቶቢሶች ላይ የተወሰደዉ እርምጃ ድጋፍ ሰጪ አውቶቢሶች በታየባቸው ክፍተት የስራ ውል እንዲያቋርጡ ተደረገ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 በአዲስ አበባ ድጋፍ ሰጪ አውቶቢሶች ላይ የተወሰደዉ እርምጃ ድጋፍ ሰጪ አውቶቢሶች በታየባቸው ክፍተት የስራ ውል እንዲያቋርጡ ተደረገ:: ከ 60 እስከ 70 የሚጠጉ ድጋፍ ሰጪ አውቶቢሶች ባሳዩት ክፍተት ውላቸው ተቋርጦ በሌሎች የመተካት ስራ እየሰራ እንደሆነ የ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖረት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ይርጋለም ብርሃኔ ከስምሪት ጋር በተያያዘ እጥረት እንዲያጋጥም የሚያደርጉት ኮድ 3 ተሸከርካሪዎች በአግባቡ ወደ ስራ አለመግባታቸው እንደሆነ ነው የገለፁት፡፡ ከአቅርቦትም ጋር በተያያዘ ሰፊ ክፍተቶች እና እንግልቶች እንዳሉ ከተጠቃሚዎች ብዙ ቅሬታ ሲነሳ ይስተዋላል፡፡

የድጋፍ ሰጪ አውቶቢሶች ላይ ዘመናዊ የመቆጣጠሪያ መሳሪያ በመግጠም ክፍተቶች የመለየት ስራ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ይህንንም ክፍተት ለመቅረፋ ወደ 15 የሚጠጉ ፕሮጀክቶች ተነድፎ እየተሰራ መሆኑን ምክትል ቢሮ ሀላፊው ማንሳታቸውን ከሀዱ የተገኘዉ መረጃ ያመለክታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *