በአፍሪካ ከ10 ሺህ በላይ የጤና ባለሙያዎች በኮቪድ19 መያዛቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ይፋ አደረገ::
አዲስ አበባ፣ሐምሌ17፣ 2012 በአፍሪካ ከ10 ሺህ በላይ የጤና ባለሙያዎች በኮቪድ19 መያዛቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ይፋ አደረገ:: ድርጅት ባወጣው ሪፖርት የሄን ያህል ቁጥር ያላቸው የጤና ባለሙያዎች በበሽታው የተያዙት በ40 የአፍሪካ ሀገራት ነው፡፡ ድርጅቱ የጤና ባለሞያዎቹ በአህጉሩ በፍጥነት እየተስፋፋ የመጣውን የኮሮናቫይረስ ስርጭት ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ወደ ኋላ የሚጎትት ፈተና ነው ብሏል፡፡ ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት የቫይረሱ ስርጭት በጣም አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን የገለፀው የዓለም ጤና ድርጅት ክስተቱ በአህጉሩ የጤና ሲስተም ላይ ትልቅ ጫና አሳርፏል ነው ያለው፡፡ በአፍሪካ እስካሁን ከ790 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ከ16 ሺህ በላይ ሰዎች መሞታቸውም በሪፖርቱ ይፋ ሆኗል፡፡ አፍሪካ ኒውስ ድርጅቱን ጠቅሶ እንደዘገበው በአብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ወረርሽኙን ለመከላከል በደረገው ጥንቃቄ የጤና ማእከላት ላይ ያለው ትኩረት በቂ የሚባል አይደለም፡፡