loading
በአፍጋኒስታን ለተቃውሞ ሰልፍ በወጡ ዜጎች ላይ በደረሰ ጥቃት የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ

አርትስ 05/03/2011

በአፍጋኒስታን  በሃዛራ ጎሳዎች የበላይነት ስር በምትገኘው ግሃዚኒ አስተዳደር የዜጎች ደህንነት ጋር በተያያዘ ለተቃውሞ ሰልፍ  በወጡ ዜጎች ላይ በተደረገ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት  3 ሰዎች ሲሞቱ 8 ሰዎች  ደግሞ ለከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ተዳርገዋል፡፡
የአፍጋኒስታን የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ምክትል ቃል አቃባይ ናስራት ራሂሚ እንደተናገሩት ጥቃቱ በአፍጋኒስታን ከተማ ፓስህቱን ኢታን አደባባይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ለተቃውሞ በወጡበት ወቅት ሰልፈኞቹን አነጣጥሮ የተፈፀመ ነው፡፡
እንደቃል አቀባዩ ገለፃ የተቃውሞ ሰልፉ ከሚካሄድበት 200 ሜትር ርቀት ላይ የፍተሸ ስራ ሲያካሂዱ የነበሩ የፀጥታ ሃይሎችም የጥቃቱ ሰለባዎች ሆነዋል፡፡
ጥቃቱ ከመፈፀሙ በፊት  የታሊባን ታጣቂዎች በርካታ የመንግስት ወታደሮችን በምዕራብ ፋራህ እና በምስራቅ ግሃዚኒ ግዛቶች  ውስጥ ቢያንስ 37 የአካባቢው ፖሊሶች እና 20 የመንግስት ታጣቂዎች መገደላቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
ካለፈው  እሮብ ጀምሮ  በተጠቀሱት አካባዎች ውጊያዎች የቀጠሉ ሲሆን፥ ቀውሱ የብሄር ግጭት ቅርጽ እንዳይዝ ስጋት ሆኗል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *