loading
በኢራን በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ በርካቶች ቆስለዋል

አርትስ 17/03/2011

ኢራን ውስጥ በርእደ መሬት መለኪያ 6.3  የሆነ የመሬት መንቀጣቀጥ ተከስቶ ከ700 በላይ ሰዎች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡

የኢራኑ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሮሀኒ የነፍስ አድን ሰራተኞቻቸውን በሚችሉት ፍጥነት ሁሉ የአደጋው ተጠቂዎችን እንዲታደጉ አስቸኳይ ጥሪ አድርገዋል፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው አደጋው የተከሰተው ኢራን ከጎረቤቷ ኢራቅ ጋር በምትዋሰንበት ምዕራባዊ የሀገሪቱ ክፍል ነው፡፡

የአካባቢው አስተዳዳሪ ሁሻንግ ባዝቫንድ እንደተናገሩት እስካሁን ወደ ሆስፒታል ከገቡት 700 ሰዎች መካከል 18ቱ ተኝተው እየታከሙ ሲሆን ቀሪዎቹ የመጀመሪያ እርዳታ ተደርጎላቸው ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል፡፡

ርእደ መሬቱን ተከትሎ በአንዳንድ አካባቢወች የመሬት መንሸራተት እየተከሰተ በመሆኑ አሁንም አደጋው እንዳይስፋፋ ስጋት ፈጥሯል፡፡

ኢራን ባለፈው ዓመት በደረሰባት ከባድ ርእደ መሬት ሳቢያ ከ600 በላይ ዜጎቿን በሞት ማጣቷ ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *