በኢሮፓ ሊግ አርሰናልና ቼልሲ ተጋጣሚዎቻቸውን ሲያሸንፉ ኤስ ሚላን ተረቷል
በኢሮፓ ሊግ አርሰናልና ቼልሲ ተጋጣሚዎቻቸውን ሲያሸንፉ ኤስ ሚላን ተረቷል
አርትስ ስፖርት 16/02/2011
ትናንት ምሽት በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች የኢሮፓ ሊግ የምድብ ሶስተኛ ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡
አርሰናል ወደ ፖርቹጋል አቅንቶ ከ ስፖርቲንግ ሊዝበን ጋር ጨዋታውን አድርጎ በዳኒ ዌልቤክ ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 በመርታት የምድቡን መሪነት በዘጠኝ ነጥብ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በአጠቃላይ የኡናይ ኢምሪ ቡድን በተከታታይ 11 ጨዋታዎች በማሸነፍ የድል ጉዞው ገፍቶበታል፡፡
ቼልሲ ደግሞ በስታንፎርድ ብሪጅ የቤላሩሱን ባቲ ቦሪሶቭ አስተናግዶ በእንግሊዛዊው ወጣት ተጫዋች ሮበን ሎፍተስ ችክ ሶስት ግቦች ታግዞ 3 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል፤ የምድቡን መሪነትም በዘጠኝ ነጥብ አስቀጥሏል፡፡
በምሽቱ ከተደረጉ ጨዋታዎች መካከል ኤስ ሚላን በሜዳው በሪያል ቤቲስ 2 ለ 1 ሲሸነፍ፤ ሌብዝህ 2 ለ 0 ሴልቲክ፣ ሬንጀርስ 0 ለ 0 ስፓርታክ ሞስኮ፣ ሲቪያ 6 ለ 0 አኪሻርስፖር፣ ዜኒት ፒተርስበርግ 2 ለ 1 ቦርዶ፣ አንደርሌክት 2 ለ 2 ፌነርባቼ፣ ቪያሪያል 5 ለ 0 ራፒድ ቬና፣ ማርሴ 1 ለ 3 ላዚዮ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡